ከፊትአውራሪ በሪሁን ጋር ሦስት ቀን ያህል ከቆየሁ በኋላ እርሱ ከጦር ግንባር ስለሚሠፍር አደጋ እንዳይደርስብኝ ወደ ደጅአዝማች ነጋሽ ወርቅነህ ሠፈር እንድሄድ ተደረገ። ቀደም ብሎ ከራስ አያሌው ብሩ ሠፈር ወደ ወንድሙ ሄዶ የነበረው የፊትአውራሪ በሪሁን አደመ ትንሽ ወንድም በዝኀብህ አደመን ከዚሁ አገኘሁትና የማውቀው ዝመድ በማግኘቴ ተደሰትሁ። ቢሆንም እንድንጓጓዝበት የተሰጠችን አንዲት በቅሎ ስለነበረች እርሱ እንደትልቅነቱ ከኮረቻው ላይ ይቀመጥና እኔ እየተፈናጠጥኩ እንጓዛለን። በቅሎ የሚይዝ ሰው ያልተሰጠን ስለሆነ ጉዟችንን ጨርሰን ከሠፈር ስንደርስ በቅሎይቱን…
Keep reading with a 7-day free trial
Subscribe to Aksum Review of Books to keep reading this post and get 7 days of free access to the full post archives.