ማንኛውም ሰው የሕይወት ታሪኩን ቢጽሕፍ ለተከታዩ ትውልድ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ።
ዳሩ ግን በልዩ ልዩ ምክንያት የተነሣ እንዲህ ዓይነቱ ታሪክ በሀገራችን በሰፊው የተልመደ አይደለም። ጠቃሚ ይሆናል ብዬ በገመትሁት መንገድ የእኔን የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው በአጭሩ አቅርቤያለሁ።
ይህን ጽሑፍ ለመጽሐፍ የገፋፋኝ በጥር ወርኅ ፲፱፻፸፩ ዓመተ ምሕረት የደርግ አባል የነበረ ሽአለቃ መልአኩ ተፈራ የሚባል የጊዜው ባዕለሥልጣን በልዩ አፋኝ ጓዶቹ ከአዲስ አበባ አስይዞ ጐንደር ወስዶ ሊገድለኝ ያደረገው ሙከራ በደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ መክሸፉ ዋናው ምክንያት ሲሆን ፣ ጐንደር ዋና አስተዳዳሪ በነበርሁ ጊዜም የገጠሙኝ ችግሮችና ለመውጣት ያደረግሁት ትግልም ቀላል ስላልነበረ ሁኔታውን ለማጤን እንዲቻል አንባቢን ጋብዣለሁ።
ማውጫ
፩ የትውልድ ሐረግና እድገት ፡ ከ፲፱፻፳ እስከ ፲፱፻፴፯ ዓመተ ምሕረት
፪ የትምህርት ዘመን
፫ በትምህርት ሚኒስተር ባልደረባነት ፡ ከ፲፱፻፵፬ እስከ ፲፱፻፶ ዓ፡ም
፬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባልደረባነት ፡ ከ፲፱፻፶ እስከ ፲፱፻፷፯ ዓ፡ም
፭ በሳውዱ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ ጉዳይ ፈፃሚ
፮ በሱዳን ከሰላ የኢትዮጵያ ዋና ቆንስል
፯ በየመን ረፐብልክ የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባዕለሙሉ ሥልጣን አምባሰደር
፰ በጐንደር ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪነት ፡
ከመስከረም ፲፭ ፲፱፻፷፰ ዓ፡ም እስከ ነሐሴ ፲፭ ፲፱፻፷፰ ዓ፡ም
፱ በሽአለቃ መልአኩ ተፈራ የተፈፀሙብኝ የአፈና ወንጀልና አተራረፌ
፲ ስለጐንደር ሕዝብ ታላቅነትና ብርታት